ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከቃና ጋር በተያያዘ የተለያዩ ግጭቶች እየተመለከትን እንግኛለን፡፡ ያልታጠቡ ልብሶች፡ ያልታጠቡ የቤት እቃዎች ፡ ያልተስተካከሉ ቤቶች እየበዙ ነው፡፡ ልጆች ከበቀናት መካከል፡ ከገመና ፡ ከሞጋቾች ይልቅ ኪኒና ጉኒ ፡ ዛራና ቻንድራ፡ ጥቁር ፍቅር ወዘተርፈ ማለት አብዝተዋል፡፡
የቴሌቪዥን የቻናል መለዋወጫዎች ከምንጊዜውም በላይ ተፈላጊ ሆነዋል፡፡ ይህ ያልታሰበ ስኬት የቴሌቪዥን ጣብያው ባለቤቶችም ያልጠበቁት ስኬት እንደሆነባቸው ለመገመት አያዳግትም፡፡
ታድያ በአብዛኛዎቹ የቴሌቪዥን ተከታታይ ፊልሞች የሚሰተዋሉት ድርጊቶች እና ቃላት የኛን በሀል እና ልምድ ያላማከሉ ናቸው ሲባል በብዛት እናደምጣለን፡፡
ይሁንና የዛሬው መነሸዬ የዝግጅቶች ይዘት እና ጭብጥ ላይ ለማውራት ሳይሆን - በየቤቱ በየሰፈሩ እያሳደረ ያለውን ተጽእኖ ለማመላከት ነው፡፡
ምናልባት እግር ጥልዎ ቤት ሲገቡ -አልጋዎት ሳይነጠፍ ፡ የቴሌቪዥኑ ድምጽ ያለ ልክ ተ ከፍቶ ቢደርሱ - እንዳይደበሩ ጉዳዩ ቃና ነው፡፡
ማናልባትም ህፃን ልጅዎ ያለወትሮው ለሊት ለሊት እንቅልፍ ቢነሳዎ ወይም ያለወትሮው ምግብ ምግብ ቢልብዎ -ይህ ቃና ነው፡፡
ሚስትዎ- ያለወትሮዋ ብዙም የማታዘወትረው ቤት እየዋለች -ቆይታ ብትመጣ ምናልባትም በክፍል …. የትንተና ፕሮግራም ላይ የራሳዋን እይታ ለማቅረብ ስለሆነ የተለየ ነገር ሳይሆን -ጉዳዩ ቃና ነው፡፡
በጠቅላላው ሰራተኞች ስራ ከመቀጠራቸው በፊት ፡ ቤተሰብ ይበዛል? ህፃናት ልጆች አሉ ? የተለያዩ ማሽኖች አሉ ካሉ በሁዋላ ፡ ቃና በበቂው ይከፈታል ብለው መጠየቃቸው እንደማይቀር ይገመታል፡፡