አዎ የማወራው ስለቦሊውድ ወይም ኖሊውድ ሳይሆን ስለኛው "
አበሽ- ውድ " ነው፡፡
በቅርቡ አንድ የጸጉር አስተካካዬ ወረፋ በዛበትና የኔ ተራ ደርሶ ጠጉሬ ከመጎማመዱ በፊት አንድ ጥጌን ይዤ ዘመን ያለፈባቸውን መጽሄቶች አገላብጣለሁ፡፡ መቼም የዘንድሮ መጽሄት ውስጥ ቁምነገር ለማግኘት በጣም ማገላበጥ ይጥቃል እና ሁሌም ወደምወደው የፊልም አምድ አመረሁ፡፡
የሚመረቅ ፊልም ለመመልከት ገብቶ የገጠመውን ጸሀፊው እያዋዛ የስነብበኝ ገባ፡፡ ተመቸኝ እና እኔም ትኩረቴን ሰጠሁት፡፡ ቀጠለ ድንገት በፊልሞቻችን ላይ የሚታዩ በተለይ የተዋናይት ቀለም መረጣ ላይ አተኮረ፡፡ ስለቀለም ምርጫዎቻችን ወደ አንድ አቅጣጫ ማዘንበል ተነተነ፡፡
ኤጭ አንዳንድ ሰው አልኩ በልቤ!
ስለመሪ እንስት ተዋናይት የቀለም ምርጫ ለማስረዳት ይጠቅሙኛል ያላቸውን ማስረጃዎች በሙሉ ዘረዘረ፡፡ ታድያ ባንድ ወቅት ጥሩ ወዳጄ የነበረ የህንድ ዜግነት ያለው ሰው በህንድ ሀገርም ይህ ችግር እንደሚንጸባረቅና በብዛት የሚመረጡ የፊልም ባለሞያዎች ቀለም ነጣ የሚሉ እንደሆነና መልካቸው ጠየም ያሉት እራሳቸውን ለማቅላት እስከ ቀዶ ህክምና የሚደርስ ህክምና እንደሚያደርጉ የነገረኝ ትዝ አለኝ፡፡
ያኔ ወይ የህንድ ሴቶች በዬ ነበር!!
ይህን ጥሁፍ ከተመለከትኩ በሁዋላ የሴት እንስቶችን በህሊናዬ መመልከት ጀመርኩ፡፡ መጀመርያ አይ ሊሆን አይችልም አልኩ፡፡ እንዴት ሲደረግ የጥቁሮች መመኪያ የነጣነት ተምሳሌት በሆነች ሀገር አይደረግም አልኩ !!
ታድያ እውነታው ከፍላጎቴ በተቃራኒው ሁኖ አገኘሁት፡፡ ጠየም የሚሉ እንስቶች በብዛት የእኩይ ገጠ ባህሪያትን ወክለው በብዛት እንደሚጫወቱና እንደ አደይ አበባ አንዴ ታይተው እንደሚጠፉ አወቅኩ፡፡
ለዚህ ማሳያ የሚሆን አንድ የማስታወቂያ በቅርብ አየሁ !! ጠይà የቤት ሰራተኛ ፡ ትንሽ ፈካ ያለችው የቤት እመቤት ፡ ቀይዋ ስለመልኩዋ ማማር፡፡
በቃ ተስፋ ቆረጥኩ!! እውነትም አለ ማለት ነው፡፡ ከዚህ አለምን ካጠቃ የዘረኝነት ደዌ አምላክ ይፈውሰን አሜን!!!

No comments:
Post a Comment