Sunday, January 31, 2016

የመጀመርያ ፍቅረኛ እውነት አይረሳም??




መቼም ስለመጀምርያ ፍቅረኛ ሲነሳ ሁላችንም የተለያየ አስተሳሰብ አለን፡፡ አንዳንዶቻችን ስንጸልይም አምላክን የመጀመርያችን የመጨረሻችን እንዲሆንልን እንለምናለን፡፡ በኩራት ያገባነው የመጀመርያ ፍቅረኛችንን መሆኑን እንናገራለን፡፡ ላንዳንዶቻችን የመጀመርያ ፍቅራችን ፍቅርን ሀ ብለን የመጀመርያችን እንደሆነ ከዝም ሁ ሂ እያልን እንቀጥላለን እንላለን፡፡ ስለዚህ መጀመርያችን የጉዞአችን መነሻ እንጂ መጨረሻ አይደለም እንላለን፡፡
ስለመጀመርያ ፍቅረኛቸው በብዛት የሚያወሩት ሴቶች ናቸው፡፡ በብዛት በተለይ አሁን ባላቸው ህይወት ደስተኛ ካልሆኑ ወደድሮው የመመለስ አዝማሚያ ይታይባቸዋል፡፡ ነገር ግን ብዙ የወነድ ጉዋደኞቼም ስለ መጀመርያ ፍቅረኛቸው ደጋግመው ያነሳሉ፡፡
የመጀመርያ ሁሌም የመጀመርያ ነው ስለዚህ በቀላሉ አይረሳም፡፡ ነገር ግን ሁሌም በመልካም ይነሳል ማለት አይደለም፡፡ ለምሳሌ በወጣች በገባች ቁጥር በቅናት ድብን እያለ ሲጨቃጨቅ የሚውል የመጀመርያን ፍቅረኛ በመልካም የሚያነሳ ማነው?
ገናለገና አብረሃት ስትሄድ ያየዋት ማናት ፡ ብለህ ብለህ ደግሞ ከእህቴ ጋር ትደዋወልልኝ ጀመርክ ብላ እርር ድብን ከምትል ጋር የነበረውን እያስታወሰ ፡ አይ እሱዋ የሱዋስ አይጣል ነው የማይል ማን አለ፡፡
በአንጻሩ ከራሱ አስቀድሞ ለርሱዋ የሚያስብላትን፡ ባሌለ አቅሙ ፍቅር ብቻ የሚመግባትን ወንድ የምትረሳ ሴት እርሱዋ ማነች? የሚገርም ፍቅር የምስሰጠውን ፡ የዛሬ መደሰታቸውን ብቻ ሳይሆን ስለወደፊት የኑሮ እቅዳቸው የምትጨነቅ ነገር ግን በኑሮ ምክንያት የተለችውን የመጀመርያ ፍቅረኛውን የማያነሳ ማን አለ፡፡
በጠቅላላው የመጀመርያ ፍቅር የማይረሳ ትዝታ የሚኖረው ቆይታው መልካም ከነበረ ብቻው ነው፡፡ ነገር ግን በብዛት በወንዶች ዘንድ የመጀመርያ ስለሆነኩ አልረሳም -የሚል ጠንከር ያለ እምነት ቢሆንም -እውነታው ግን ያሳለፍነው ጊዜ ጣፋጭነት ይወሰናል ነው፡፡

የጫት ቤት ወግ!!




አብዛኛው ጫት ቤት ተጠቃሚ ለምን ጫት ቤት እንደሚሄድ ብትጠይቁት የሚሰጣችሁ ምላሽ ተቀራራቢ ነው፡፡ ጫወታው ይመቻል ነው፡፡ እውነትም ጫት ቤት ለየት ባለ መልኩ ከሁሉም  የስራ ዘርፍ የተለያዩ ሰዎችን ማግኘት የተለመደ ነው፡፡ አስተማሪው ፡መሃነዲሱ ፡ ሀኪሙ  ደላላው ፡ ቀፋዩ ፡ፖሊሱ ፡ ሌባው በአንድነት የሚገናኝበት ቦታ ነው፡፡
ታድያ እነዚህ ጫት ቤት ውስጣ የማይጠፉ ወሬ አዋደው የሚያወሩ ፡ በአብዛኛው በቅፈላ ስራ የተሰማሩ አጫዋቾች አሉ፡፡ እነዚህ አጫዋቾች ወደ ጫት ቤት የሚገቡት ቤሳቤስቲን ሳይዙ ነው፡፡ ከተገኘ ከታዳሚዎቻቸው ካልሆነም ከ ባለጫት ቤቶቹ በማይከፈል ዱቤ ይቅማሉ፡፡ አላማቸው ማሳቅ ነው፡፡ ስለዚህ እነሱጋ ስርአት ብሎ ነገር የለም፡፡ ደጋግሞ የሚጋብዛቸው የገባው፡ ያራዳ ልጅ ፡ አሪፍ ፤ የሚሉት ስሞች ይወርድለታል ፡፡ ሠላምም ሲሉ በተለሳለሰ አጨባበጥ ፡ በአብዛኛው ከመቀመጫቸው ተነስተው ነው፡፡
የማይፈለጠው የራሱን ቅሞ የሚሄደው ግን በአብዛኛው ፡ ያልገባው፡ ጤባ ፡እርጥብ ፡ አቦ ይሄ ሰው አይመቸኝም ….የመሳሰሉት ቃላት ይወደወሩበታል፡፡
ብዙ ግዜ የሚገርመኝ የጫት ቤቶቹ ደረጃ እና የሚገቡበት ሰዎች አለመጣጣማቸው እና ይህንንም ሰዎቹ አለማስተዋላቸው ነው፡፡ ለነገሩ ከቦታው ሳይሆን ትልቁ መፈላለግ ያለው ከሰዎቹ ነው፡፡ በተለይ አባዛኛዎች የጥበብ ሰዎቻችን ስለጥበብ ጫት ቤት ካልሆነ ማውራት አይመቻቸውም( ታድያ እዚህ ጋ አብዛኛው ማለቴ ይሰመርልኝ፡፡ ይሀው ችግር ያስቸገራቸው እና አጋር ያጡ ጠንከር ያሉ ጥበበኞች እንዳሉ ልብ ይሉዋል፡፡)
ጫት ቤት ውስጥ የማያወራ የወግ ርእስ የለም፡፡ ስለፍቅር፡ ስለትዳር፡ ስለኑሮ ውድነት፡ ስለ ጥበብ፡ ስለግድብ፡ስለስደት ፡ ኩዋስ፡ ተቃራኒ ጾታ፡ ፖለቲካ ፡ እንዲሁም ፡ ስለአዳዲስ ክስተቶች… በሙሉ ይወራል፡፡
ታድያ ደስ የሚለው ስለሚወራው ርእስ በቂ እውቀት ይኑረውም አይኑረውም ሁሉም ስለ ሁሉም ነገር ያወራል፡፡ አለማውራት የሚያስቀጣ እስኪመስል ድረስ ይወራል፡፡
ሚርቃና የ መቃም የክላይሜክስ ጥግ ሲሆን አብዛኛው ሰው ጫትን የሚቅመው ይህንን ደረጃ ለመንካት ነው፡፡ ታድያ የየሰዉ የሚርቃና አይነት ይለያያል፡፡ አንዳንዱ ሲመረቅን ስለተለያዩ ሀሳቦች በበለጠ ማውራት ሲፈልግ አንዳንዱ ጭራሽ አብሮት ሲቅም የነበረውን ሰው ጥርቅም አድርጎ ይዘጋዋል፡፡ አንዳንዱ የፈጠጠ አይኑን እያቁለጨለጨ አካባቢውን ይመለከታል፡፡
በጣም ወጣ ያሉ የሚርቃና አይነቶችም ይስተዋላሉ፡፡ ከነዚህ ውስጥ ለየት ያሉትን ላንሳ - አንዳንዶች ሲበዛ ቸር ይሆናሉ ከመርቀናቸው በፊት ወይ ፍንክች ይሉ የነበሩት ፡ ከሚርቃና በሁዋላ ያልመረቀነ ሰው ካዩ ጫት ካልገዛን ብለው ያስቸግራሉ፡፡ የለባቸው ዱቤ አንድ በአንድ ትዝ ስለሚላቸው ካልከፈሉ ወይ ኪሳቸው ያለው ብር ካላለቀ ምንም እርካታ የላቸውም፡፡
አንድ በጣም የሚያስቅ ሚርቃና ያለው ሰው ደግሞ ሁሉንም ቀዳዳዎቹን መዝጋት ይጀምራል፡፡ ብርድ እንዳይመታው መሆኑን ስትሰሙ ፈገግ ያድርጋል፡፡
የጫት ተጠቃሚ ሴቶች ቁጥር እንደወንዱም ባይሆን  ትንሽ የማይባል ሆኑዋል፡፡
ጫት ቤት በብዛት የሚሰማ ነገር ቢኖር የሚራዘም ቀጠሮ ነው፡፡ ምን ባክህ ቤተሰብ ጋር ሄጄ ሳልመለስ ቀረው ፡ በጣም ሩቅ ቦታ ነኝ ነገ እናድርገው፡፡ ….የመሳሰሉትን ንግግሮች መስማት የተለመደ ነው፡፡
ብዙዎች እነደሚናገሩት ጫት የሚጀምሩት በጉዋደኛ ግፊት ሲሆን ወደ ሱስነት መቀየሩን መቀበል ይከብዳቸዋል፡፡ በብዛት ማቆም ቀላል መሆኑን ግን ግዜኣቸውን የሚያሳልፉበት ሌላ ቦታ እንደሚያጡ ያስረዳሉ፡፡ ከዚህም በላይ ጫት ምንም አይነት የጤና ጉዳት እንደሌለው አጥብቀው ይከራከራሉ፡፡
የጫት ሱሰኝነትን የበለጠ የሚያስረዳልኝ ማመላከቻ አንድ ጉዋደኛዬ ነው ፡፡ ይሀው ጉዋደኛዩ የ ፋርማሲ ዲግሪውን ሲያጠናቅቅ የስራው ጫት በጤና ላይ በተለይ በወሲብ ህይወት ላይ ያለውን አሉታዊ ተጽእኖ ሲሆን ያቀረበው ጽ ሁፍም በአስተማሪው ተወዶለት ጥሩ ውጤት አስገኝሎታል፡፡ አስተማሪውም በጽሁፉ ያልተሸፈኑ ሌሎች ጥናቶችን እነዲያከናውኑ ሌሎች ተማሪዎችን ይገፋፋሉ ፡፡ ታድያ ይህ ጉደኛዬ ጥናቱን ሲያከናውም ሆነ ጥናቱን ከጨረሰ በሁዋላ በአቃቃሙ ላይ ምንም ለውጥ አላሳየም፡፡ ይልቁኒም ጨመረበት እንጂ፡፡
ቸር እንሰንብት!!

Saturday, January 30, 2016

ማሳጅ ወይስ የወሲብ ቤት?



ማሳጅ ወይስ የወሲብ ቤት?
አዲስ አበባ ውስጥ እስከቅርብ ድረስ ተስፋፍተው ከነበሩ የንግድ ቦታዎች ውስጥ አንዱ የማሳጅ ቤት ነበር፡፡ ማሳጅ እጅግ ተወዳጅ የሆነ ሳይንሳዊ ዘዴን ተጠቅሞ ሰውን ከድካም፡ ከጭንቀት እንዲሁም ከተለያዩ በሽታዎች የሚፈውስ ድንቅ ጥበብ ነው፡፡ ስለዚህ የሙያው ባለቤቶች ሰዎች ማሳጅ እንዲጠቀሙ እጅጉን ይመክራሉ፡፡
አብዛኛው ሰው ማሳጅን ተጠቅሞ የነበረ ስለማሳጅ አገጣሚው ብዙ ሲያወራ አይታየም፡፡ ምክንያቱ ደግሞ በአብዛኛው አዲስ አበባ ላይ የነበሩ የማሳጅ ቤቶች የወሲብ መፈጸሚያ ስፍራዎች በመሆናቸው ነው፡፡ ስለዚህ ስለማሳጅ ቤት መሄድ ካወሩ ወሲብ ስለመፈጸማቸው ታወቀ ማለት ስለሆነ ማንም አያወራም፡፡ ስለዚህ እኔ ላውራ፡፡JJ
የማሳጅ ስልጠና የሚሰጡ ድርጅቶች በሙሉ ሲያሰለጥኑ ስለ ማሳጅ ዲሲፕሊን አያሰለጥኑም፡፡ አብዛኛዎቹ አሰልጣኞች የሰለጠኑትን ቴክኒካዊ ትምህርት ብቻ የሚያሰለጥኑ ናቸው፡፡ ስለዚህ አብዛዎቹ ሰልጣኞች ማሳጅ ሲሰሩ የሚከተሉት ነገር የለም፡፡
ለነገሩ በየማሳጅ ቤቱ የሚገኙ ማሳጅ ከሚሰሩ ሴቶች ውስጣ በትክክል የሰለጠኑትም በጣም ጥቂቶች ሲሆኑ እነሱ በቃል የነገሩዋቸው ሌሎች መልከመልካም ቁመና ያላቸው ለግላጋ ወጣቶች በጥንቃቄ በባለቤቶች እየተመረጡ የሚገቡበት የስራ መስክ ሆኖ ነበር ማሳጅ፡፡
ታድያ እነዚህ ሴቶች ማሳጅ መስራት ሳይሆን የሚያደርጉት ስሜት ማነሳሳት ነው፡፡ ሲጀምር የሚለብሱት ሽራፊ ጨርቅ በቅጡ ገላቸውን መሸፈን አይችልም፡፡ ስለዚህ የሰውነታቸው መገላለጥ ፡ ማሳጅ የሚሰጥባቸው ቦታዎች ጥበት እና ጨለማነት ፡ ከመጠን በላይ የሚለቀቁት ሙዚቃዎች ፡ የልጆቹ ንግግር ፡ በሙሉ ሆን ተብለው የተዘጋጁ ነቸው፡፡
በብዛት የማሳጅ ቤት ተጠቃሚዎች -የውጪ ሃገር ነዋሪዎች እና ወደሀገር ቤት የተመለሱ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵውያን ሲሆኑ ቁጥራቸው በዛ ያሉ የንግድ ማህበረሰቦችም የዚህ አገልግሎቶች ተጠቃሚዎች ናቸው፡፡ ይሁንና በጣም ታቃቂ ሰዎችም ይህን አገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸውን የዚህ አገልግሎት ሰጪ የሆኑ እንስቶች ይናገራሉ፡፡
ማሳጅ ቤቶች በኣንድ ሰሞን በአዲስ አበባ ቁጥራቸው ከመጠን በላይ በዘቶ ነበር፡፡ በያንዳንዱ ሰፈር መግቢያ ላይ ፡ በያንዳንዱ መጠጥ ቤት ጎን አንድ ማሳጅ ቤት ተከፍቶ ነበር፡፡
የአገልግሎት ታሪፍን በሚመለከት -ኖርማል ማሳጅ ለመሰራት የሚጠየቀው 200 ብር ሲሆን ይህ ትክክለኛ ማሳጅ የሚጠቀም ሰው የሚከፍለው ታሪፍ ነው፡፡ ትክክለኛ ማሳጅ የሚጠቀም ሰው ከሁለት ሶስት ግዜ በሁዋላ የሚሰራው አያገኝም፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ቀላል ነው፡፡ ማሳጅ ብቻ ስለሚጠቀም አንደኛ ጉልበት ያስወጣል ፡፡ ሁለተኛ ጠቀም ያለጥቅም ያስመልጣል፡፡
የማሳጅ ቤት ሴቶች እንደሚመሰክሩት ለሎች አገልግሎቶች የሚያስከፍሉት ዋጋ ከደንበኛ ደንበኛ ይለያያል፡፡ የውጪ ዜጋ ከሆነ እስከ 1000 ብር ያስከፍላሉ፡፡ ነጋዴ ከሆኑም እንዲሁ ፡፡ ለሌሎች ግን ዋጋ እነደሚቀንሱ ይናገራሉ፡፡
የተለያየ ልምድ እና ፍላጎት ያላቸው ወንድ እና ሴቶች እንደሚያጋጥማቸው የሚገልጹት እነዚህ የማሳጅ ቤት አገልግሎት ሰጪዎች ሁሉንም እንደ አመጣጡ መመለስ ካልቻሉ በባለቤቶች ከፍተኛ ተጽእኖ እንደሚደርስባቸው ይናገራሉ፡፡ ከስራው አዋጪነት የተነሳ ብዙ ብር በማውጣት የሚገርሙ ቤቶች የሚከራዩ ባለቤቶች ሰው የመለዋወጥ ፍላጎት እንዳላቸውና አንዲት የማሳጅ ሰራተኛ በቤታቸው ከ 3-6 ወር ብቻ መስራት እንደሚፈቀድ ከዚህ ጊዜ ካለፈ ግን ቤት መቀየር እነደሚገባቸው ይናገራሉ፡፡
ይሁንና የማሳጅ ሞያ እጅግ የተከበረ ሞያ መሆኑን በመገንዘብ ሞያውን በትምህርት አዳብረው ለመስራት ተዘጋጅተው ፡ሲሰራበት የነበረውን ቅጥ ያጣ ስርአት በመቃወም ብቻ ስራ ያልጀመሩ ፡ ጀምረውም ፈተና ስለበዛባቸው ስራውን የተዉ የማሳጅ ባለሞያዎች እንዳሉ ሁሉም ሊገነዘብ ይገባል፡፡

የአረብ ሀገር ሴቶቻችን እና የፍቅር ጫወታ!!





በቅርብ አንድ ወዳጄ ከቅርብ ግዜ ወዲህ ቢዚ ቢዚ ሲያበዛብኘን እንዲሁም የኑሮው ሁኔታ ለውጥ ሲያሳይ፤ ከወትሮው ብድር ጥያቄው ቀነስ ቢያደርግብኝ ፡ ተገናኘተን ስለለውጡ ለመነጋገር ተስማማን-
ስንገናኝ ሰላምታ ከተለዋወጥን በሁዋላ- አንድ ነገር አስተዋልኩ - የሚገርም ሳመሰንግ ስልክ ገዝቱዋል፡፡-ከስልኩጋም የተለየ ዝምድና ፈጥሮል፡፡
የዚህ ለውጥ ነገር ሚስጥሩን ለማወቅ -በጥያቄ ጀመርኩ "ምን ተገኘ ባክህ እንዲህ የጠፋሀው ? ደሞ ውበቱን ደፍቶብሃል!!"
"ምን ባክህ ጊዜ ጠፋ" - አለኝ ስልኩን እየነካካ
የስልኩን አዲስነት እና ጥሩነት እያደናነቅኩኝ ምን አዲስ ነገር እንደተገኘ ጠየኩት፡፡
አዲስ የስራ ዘርፍ እንደተገኘ ና በጣም አዋጭ እና ቀላል እንደሆነ የሚያስፈልገውም ስልክ ብቻ መሆኑን ነገረኝ፡፡ የሚነግረኝ ነገር የበለጠ ለመወቅ የሚያጉዋጋ በመሆኑ የበለጠ እንዲነግረኝ ጋበዝኩት
ስራው የሚሰራው በቫይበር እነደሆነና ወጪው የቴሌ ካርድ መሆኑን እርሱም ቢሆን በደንበኞቹ እንደሚከፈል ነገረኝ፡፡ ጉዳዩ የበለጠ ስላጉዋጉዋኝ  የስራውን ምንነት እንዲነግረኝ ጠየኩት

"ሥራውማ ከ አረብ ሀገር ሴቶች ጋር ፍቅር መስራት ነው!! "አለኝ፡፡ ነገሩ ግልፅ ስላልሆነልኝ እንዲያስረዳኝ ጠየኩት፡፡
"ምን መሰለህ "- ቀጠለ -"በአብዛኛው የ አረብ ሀገር ሴቶች ለብዙ ግዚያት ታፍነው ነው የሚቆዩት ፡፡ ስለዚህ ስለፍቅር ስለወሲብ በደምብ የሚያወራቸው ሰው ይፈልጋሉ፡፡ ስለዚህ መጀመርያ የሚስብ ቁመና ያለው ምስል የያዘ የፌስቡክ አካውንት ትክታለህ ፡፡ ከዚያም በየሀረብ ሀገር ያሉ ሴቶችን ታጠምዳለህ፡፡ ሁሉም ሴቶች እኩል ላየፈልጉ ይችላሉ፡፡ አንዳንዶች ስለሀገር ማውራት ይወዳሉ ፡፡ አንዳንዶች ስለሀያማኖት ማውራት ይወዳሉ ፡፡ አብዛኛዎቹ ግን ስለ ስክስ ማውራት ይወዳሉ፡፡ ስለሴክስ የሚያወሩት ግን እስከመጨረሽያው ነው ፡፡ አብዛኛዎቹ የስልክ ሴክስ ማድረግ ይፈልጋሉ ፡፡ ቢያንስ በሁለት ቀን አንዴ የስልክ ሴክስ መድረግ ትፈልጋለች ስለዚህ የኔ ስራ እነሱን መርዳት ነው ፡፡ ከዛማ የ ምትፈልገውን መጠየቅ ነው ይደረግልሃል፡፡ የሚገርምህ አንዳንዶቹ ሀገር ቤት ጉዋደኛ አላቸው ግን የሚያወሩዋቸው ስለ ቤት ጣጣ ነው እንጂ ስለሴክስ አይደለም፡፡ ስለዚህ ለኛ ለኛ ተመችቶናል፡፡" እያለ ያስረዳኝ ጀመር፡፡
"ቾቤን ታውቀው የለ ያ የላይ ሰፈሩን ልጅ ፣ ሰሞኑን 5 ል ታክሲ ሊገዛነው ፡፡ ባርያው ጫት ቤት የከፈተው ኬት አምጥቶ ይመስልሃል?"
ከውስጤ አዘንኩ፡፡ ሴቶቻችን ይህንን ገንዘብ ለማመጣት የሚከፍሉትን መስዋትነት አሰብኩና የምር ከውስጤ አዘንኩ፡፡

ለምን ሩዋጮቻችን ብቻ?



መቼም ሁላችንም እንደምናየው የሩዋጮቻችን አይበገሬ ነት ጎልቶ የወጣ ነው ፡፡ በየሄዱበት ድል በድል ላይ ማመጣት የግላቸው አርድርገውታል፡፡ ከ አበበ  ፡ ከማሞ ፡ ከምሩጽ ፡ከኀይሌ ፤ ከቀነኒ ኬኛ ……ከሴቶቹም -ሳቂተዋ ደራርቱ፡ መሰረት፡ ጥሩነሽ፡ ገንዘቤ..
እንግዲህ የሩጫዎቻችንን ይህል ሌሎች ነገሮቻችን ያንን ያህል አለመውጣታቸው ያሳዝናል፡፡
ሙዚቃችን የሀገራችንን ያህል እድሜ ያለው እድሜ ጠገብ ነው፡፡ በሙዚቃችን ያነገስናቸው ጀግኖች ብዙ ናቸው፡፡ ያንኑ ያህል ሙ ዚቃችን ከወንዝ ሊሻገር አልቻለም፡፡ ከሱዳን አልፎ አፍሪካን ማዳረስ አልቻለም፡፡
እግርኩዋሳችን የምንኮራበት እና ደረታችንን ነፍተን የምንታይበት አልሆነም፡፡ እኔ ምለው ግን ለምንድነው ተጫዋቾቻችን ይህንን ያህል ደረት የሚነፉት ? ምን ያህል በኩዋስ ዝቅ እንዳደረጉን አያውቁም ?ነው እነሱና እኛ የምናየው ኩዋስ ይለያያል?
ፊልሞቻችን አይደለም እንደነ ጋና እና ናይጄሪያ ፊልሞች አህጉር አቁዋርጠው ሊታዩ ይቅርና የሚመለከታቸውም የተወሰነ እድሜ ላይ ያለ ሰው ብቻ ነው፡፡
እንዲህ እንዲህ እያልን ባነኮቻችንን፡ ዩኒቨርስቲዎቻችንን፡ የአገልግሎት ሰጪዎቻችንን ማካተት እንችላለን፡፡
እንግዲህ  ከላይ እንደተመለከትነው  አብዛኛዎቹ ዘርፎቻችን በሀገርኛ ታጥረው የቀሩበት ምክንያት ምንድነው ነው ? ጥያቄው ምንስ ቢደረግ ይሻላል የሚለው የመፍትሄ ሀሳብ ማመንጪያ ጥያቄም ሊከተል ይገባዋል፡፡ ካልሆነ ያሉን ብርቅዬ ነገሮችን ሙዚቃዎቻችን፡ እግርኩዋሶቻችን እና ፊልሞቻችንን ሊጨምሩ ይገባል ፡፡ ለምን ዋልያ ና ቀይቀበሮ … ብቻ!!!
እንግዲህ በዋና ነት  የዚህ ችግር ምክኒያት አተያየታችን ይመስለኛል፡፡ ሌሎቹ የአፍሪካ ሀገሮች የጋራ የሆነ ምን ነገር እንዳላቸው ያውቃሉ፡፡ እኛ ግን ስለውጨው ነገር የምናውቀው ብዙ አይደለም፡፡አሁን ለማወቅ ጥረት ካደረግን በጣም ቀላል ሆኑዋል፡፡ ኢንተርኔት አለምን በጣም አቀራርቦዋታል፡፡ ስለዚህ የናይጄሪያ የእግር ኩዋስ አጨዋወት ምን ይመስላል? የጋናውያን የ ሙዚቃ ስልት እንዴት ይታያል ? ለምንስ ተወደደ? ትንሽ ሪሰርች በቂ ነው መጠየቅ፡፡
ባንኮቻችን አንድ ስታንዳርድ ቻርተር ቢመጣ የት እንደሚገቡ እኔንጃ !! እውቁ የኢኮኖሚስት ባለሙያ እስዳስታወቁት በሚቀጥሉት 5 አመታት የውጪ ባንኮች ወደ ኢትዮፕያ መምጣታቸው ግድ ነው፡፡
አያቴ እንደምትለው አሁን ምን ያደርጋል ድስት ጥዶ ማልቀስ ቀድሞ ነበር እንጂ ………. መደቆስ!!!!