ማስተወቂያዎቻችን እና ጉድፈቶቻቸው!!
በዚህ ጽሁፍ የቀረበው የማስታወቂያ አሰራር ጉድፈት
አንድ ገጽታ ሲሆን ለማስታወቂያው እንደዚህ መውረድ የተለያዩ ምክንያቶች ሊጠቀሱ ይችላሉ ፡፡ በኔ እምነት የማስታወቂያ ሰሪዎቹ የማርኬቲንግ
እውቀት ማነስ ትልቁን ስፍራ የሚይዝ ይመስለኛል፡፡ የሚያሳዝነው ይህንን የእውቀት ማነስ ለማረም የሚያስችል የተለያዩ መንገዶች ቢኖሩም
በባለሞያዎቹ ሲታሰብ አይታይም፡፡ ቀላሉ መንገድ የማርኬቲንግ ባለሞያዎችን በተወሰኑ መንገድ መጠቀም ነው፡፡ ነገር ግን አንድ በጣም
ጥሩ የ ማስታወቂያ እውቀት በትምህርት ያዳበረ የመመረቂያ ጽሁፉንም በማስታወቂያ ዙርያ የሰራ ወዳጄ በነጻ በማስታወቂያ ድርጅቶች
ለመስራት ፈልጎ እድሉን የሰጠው አንድም የማስታወቂያ ድርጅት አልነበረም፡፡እነዚህ የማስታወቂያ ባለሞያዎችም የ ማርኬቲንግ ትምርት
ሲማሩም አይታይም፡፡
በአንድ ወቅት በጣም የማከብራቸው የማስታወቂያ
ባለሞያ አንዲት በማርኬቲንግ የማስተርስ ዲግሪ ያላትን ሴት ከርሳቸው ጋር ልትሰራ ስትመጣ የፈተኑበትን መንገድ ሲናገሩ በሌሎች ተዋናዮች
ነቀላሉ የሚሰራን ትወና የሰጡዋትን እንዴት መወጣት እንዳቃታት ተናግረዋል፡፡
ሌላኛው የማስተወቂያ ባልደረባ ለተመራቂ ተማሪዎች
ልምድ እንዲያካፍል ተጠርቶ ሲናገር በአብዛኛው ማስታወቂያ የሚሰራበትን መንገድ እርሱም እንደማያምንበት እና የማስታወቂያ አስነጋሪዎቹ
ከእገሊት ጋ እንደዚህ ካልሰራችሁ አይሆንም እንደሚሉዋቸው እና እነሱም በተባሉት መንገድ እንደሚሰሩ ጠቁሙዋል፡፡
የሚያሳዝነው ዘርፉ እውቀት ና ዝግጅቱ ላላቸው
ባላሞያዎች ለመግባት ከባድ መሆኑ ነው፡፡ የትኛውንም አይነት እውቀት የትኛውንም የተለየ አሰራር ይዞ ለሚመጣ እውነተኛ የማስታወቂያ
ባለሞያ ወደስራ ለመግባት ከተራራ የከበደ ነው፡፡
በዚህ ረገድ ማስታወቂያ በተለመዱ የማስታወቂያ
አስነጋሪዎች የሚያስነግር ድርጅት ጋር የሚያስደንቅ የማስታወቂያ ሀሳብ ወስዶ ያሳያቸው የ ሽያጭና ገበያ ሀላፊ ለሃሳቡ አመንጪ በአባታዊ
ምክር አሁን እየተጠቀምናቸው ያሉት ባላሙያዎች በዘርፉ ቁንጮ የሆኑ ባለሞያዎች ናቸው ፡፡ የድርጅቱ አመራርም ይህንን ሀሳብ ባቀርብ
አይቀበለኝም ስለዚህ ምናልባት ሌላ ቦታ ሞክር አሉት፡፡
የሚገርመው አዳዲስ ድርጅቶችም አቅማቸው ሲጎለብት
ለመጠቀም የሚያስቡት እነዚህኑ ቁንጮዎቹን ነው፡፡
ስለዚህ ቁንጮቹም ትክክል እንደሆኑ እያሰቡ ባለሞያዎቹም
ሞያቸውን ተነፍገው የሀው እዚህ ተደርሱዋል፡፡ ማን ያውቃል ነገ ሌላ ቀን ነው ----ቸር እንሰንብት!!
No comments:
Post a Comment