Saturday, January 30, 2016

ማሳጅ ወይስ የወሲብ ቤት?



ማሳጅ ወይስ የወሲብ ቤት?
አዲስ አበባ ውስጥ እስከቅርብ ድረስ ተስፋፍተው ከነበሩ የንግድ ቦታዎች ውስጥ አንዱ የማሳጅ ቤት ነበር፡፡ ማሳጅ እጅግ ተወዳጅ የሆነ ሳይንሳዊ ዘዴን ተጠቅሞ ሰውን ከድካም፡ ከጭንቀት እንዲሁም ከተለያዩ በሽታዎች የሚፈውስ ድንቅ ጥበብ ነው፡፡ ስለዚህ የሙያው ባለቤቶች ሰዎች ማሳጅ እንዲጠቀሙ እጅጉን ይመክራሉ፡፡
አብዛኛው ሰው ማሳጅን ተጠቅሞ የነበረ ስለማሳጅ አገጣሚው ብዙ ሲያወራ አይታየም፡፡ ምክንያቱ ደግሞ በአብዛኛው አዲስ አበባ ላይ የነበሩ የማሳጅ ቤቶች የወሲብ መፈጸሚያ ስፍራዎች በመሆናቸው ነው፡፡ ስለዚህ ስለማሳጅ ቤት መሄድ ካወሩ ወሲብ ስለመፈጸማቸው ታወቀ ማለት ስለሆነ ማንም አያወራም፡፡ ስለዚህ እኔ ላውራ፡፡JJ
የማሳጅ ስልጠና የሚሰጡ ድርጅቶች በሙሉ ሲያሰለጥኑ ስለ ማሳጅ ዲሲፕሊን አያሰለጥኑም፡፡ አብዛኛዎቹ አሰልጣኞች የሰለጠኑትን ቴክኒካዊ ትምህርት ብቻ የሚያሰለጥኑ ናቸው፡፡ ስለዚህ አብዛዎቹ ሰልጣኞች ማሳጅ ሲሰሩ የሚከተሉት ነገር የለም፡፡
ለነገሩ በየማሳጅ ቤቱ የሚገኙ ማሳጅ ከሚሰሩ ሴቶች ውስጣ በትክክል የሰለጠኑትም በጣም ጥቂቶች ሲሆኑ እነሱ በቃል የነገሩዋቸው ሌሎች መልከመልካም ቁመና ያላቸው ለግላጋ ወጣቶች በጥንቃቄ በባለቤቶች እየተመረጡ የሚገቡበት የስራ መስክ ሆኖ ነበር ማሳጅ፡፡
ታድያ እነዚህ ሴቶች ማሳጅ መስራት ሳይሆን የሚያደርጉት ስሜት ማነሳሳት ነው፡፡ ሲጀምር የሚለብሱት ሽራፊ ጨርቅ በቅጡ ገላቸውን መሸፈን አይችልም፡፡ ስለዚህ የሰውነታቸው መገላለጥ ፡ ማሳጅ የሚሰጥባቸው ቦታዎች ጥበት እና ጨለማነት ፡ ከመጠን በላይ የሚለቀቁት ሙዚቃዎች ፡ የልጆቹ ንግግር ፡ በሙሉ ሆን ተብለው የተዘጋጁ ነቸው፡፡
በብዛት የማሳጅ ቤት ተጠቃሚዎች -የውጪ ሃገር ነዋሪዎች እና ወደሀገር ቤት የተመለሱ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵውያን ሲሆኑ ቁጥራቸው በዛ ያሉ የንግድ ማህበረሰቦችም የዚህ አገልግሎቶች ተጠቃሚዎች ናቸው፡፡ ይሁንና በጣም ታቃቂ ሰዎችም ይህን አገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸውን የዚህ አገልግሎት ሰጪ የሆኑ እንስቶች ይናገራሉ፡፡
ማሳጅ ቤቶች በኣንድ ሰሞን በአዲስ አበባ ቁጥራቸው ከመጠን በላይ በዘቶ ነበር፡፡ በያንዳንዱ ሰፈር መግቢያ ላይ ፡ በያንዳንዱ መጠጥ ቤት ጎን አንድ ማሳጅ ቤት ተከፍቶ ነበር፡፡
የአገልግሎት ታሪፍን በሚመለከት -ኖርማል ማሳጅ ለመሰራት የሚጠየቀው 200 ብር ሲሆን ይህ ትክክለኛ ማሳጅ የሚጠቀም ሰው የሚከፍለው ታሪፍ ነው፡፡ ትክክለኛ ማሳጅ የሚጠቀም ሰው ከሁለት ሶስት ግዜ በሁዋላ የሚሰራው አያገኝም፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ቀላል ነው፡፡ ማሳጅ ብቻ ስለሚጠቀም አንደኛ ጉልበት ያስወጣል ፡፡ ሁለተኛ ጠቀም ያለጥቅም ያስመልጣል፡፡
የማሳጅ ቤት ሴቶች እንደሚመሰክሩት ለሎች አገልግሎቶች የሚያስከፍሉት ዋጋ ከደንበኛ ደንበኛ ይለያያል፡፡ የውጪ ዜጋ ከሆነ እስከ 1000 ብር ያስከፍላሉ፡፡ ነጋዴ ከሆኑም እንዲሁ ፡፡ ለሌሎች ግን ዋጋ እነደሚቀንሱ ይናገራሉ፡፡
የተለያየ ልምድ እና ፍላጎት ያላቸው ወንድ እና ሴቶች እንደሚያጋጥማቸው የሚገልጹት እነዚህ የማሳጅ ቤት አገልግሎት ሰጪዎች ሁሉንም እንደ አመጣጡ መመለስ ካልቻሉ በባለቤቶች ከፍተኛ ተጽእኖ እንደሚደርስባቸው ይናገራሉ፡፡ ከስራው አዋጪነት የተነሳ ብዙ ብር በማውጣት የሚገርሙ ቤቶች የሚከራዩ ባለቤቶች ሰው የመለዋወጥ ፍላጎት እንዳላቸውና አንዲት የማሳጅ ሰራተኛ በቤታቸው ከ 3-6 ወር ብቻ መስራት እንደሚፈቀድ ከዚህ ጊዜ ካለፈ ግን ቤት መቀየር እነደሚገባቸው ይናገራሉ፡፡
ይሁንና የማሳጅ ሞያ እጅግ የተከበረ ሞያ መሆኑን በመገንዘብ ሞያውን በትምህርት አዳብረው ለመስራት ተዘጋጅተው ፡ሲሰራበት የነበረውን ቅጥ ያጣ ስርአት በመቃወም ብቻ ስራ ያልጀመሩ ፡ ጀምረውም ፈተና ስለበዛባቸው ስራውን የተዉ የማሳጅ ባለሞያዎች እንዳሉ ሁሉም ሊገነዘብ ይገባል፡፡

No comments:

Post a Comment