Sunday, January 31, 2016

የመጀመርያ ፍቅረኛ እውነት አይረሳም??




መቼም ስለመጀምርያ ፍቅረኛ ሲነሳ ሁላችንም የተለያየ አስተሳሰብ አለን፡፡ አንዳንዶቻችን ስንጸልይም አምላክን የመጀመርያችን የመጨረሻችን እንዲሆንልን እንለምናለን፡፡ በኩራት ያገባነው የመጀመርያ ፍቅረኛችንን መሆኑን እንናገራለን፡፡ ላንዳንዶቻችን የመጀመርያ ፍቅራችን ፍቅርን ሀ ብለን የመጀመርያችን እንደሆነ ከዝም ሁ ሂ እያልን እንቀጥላለን እንላለን፡፡ ስለዚህ መጀመርያችን የጉዞአችን መነሻ እንጂ መጨረሻ አይደለም እንላለን፡፡
ስለመጀመርያ ፍቅረኛቸው በብዛት የሚያወሩት ሴቶች ናቸው፡፡ በብዛት በተለይ አሁን ባላቸው ህይወት ደስተኛ ካልሆኑ ወደድሮው የመመለስ አዝማሚያ ይታይባቸዋል፡፡ ነገር ግን ብዙ የወነድ ጉዋደኞቼም ስለ መጀመርያ ፍቅረኛቸው ደጋግመው ያነሳሉ፡፡
የመጀመርያ ሁሌም የመጀመርያ ነው ስለዚህ በቀላሉ አይረሳም፡፡ ነገር ግን ሁሌም በመልካም ይነሳል ማለት አይደለም፡፡ ለምሳሌ በወጣች በገባች ቁጥር በቅናት ድብን እያለ ሲጨቃጨቅ የሚውል የመጀመርያን ፍቅረኛ በመልካም የሚያነሳ ማነው?
ገናለገና አብረሃት ስትሄድ ያየዋት ማናት ፡ ብለህ ብለህ ደግሞ ከእህቴ ጋር ትደዋወልልኝ ጀመርክ ብላ እርር ድብን ከምትል ጋር የነበረውን እያስታወሰ ፡ አይ እሱዋ የሱዋስ አይጣል ነው የማይል ማን አለ፡፡
በአንጻሩ ከራሱ አስቀድሞ ለርሱዋ የሚያስብላትን፡ ባሌለ አቅሙ ፍቅር ብቻ የሚመግባትን ወንድ የምትረሳ ሴት እርሱዋ ማነች? የሚገርም ፍቅር የምስሰጠውን ፡ የዛሬ መደሰታቸውን ብቻ ሳይሆን ስለወደፊት የኑሮ እቅዳቸው የምትጨነቅ ነገር ግን በኑሮ ምክንያት የተለችውን የመጀመርያ ፍቅረኛውን የማያነሳ ማን አለ፡፡
በጠቅላላው የመጀመርያ ፍቅር የማይረሳ ትዝታ የሚኖረው ቆይታው መልካም ከነበረ ብቻው ነው፡፡ ነገር ግን በብዛት በወንዶች ዘንድ የመጀመርያ ስለሆነኩ አልረሳም -የሚል ጠንከር ያለ እምነት ቢሆንም -እውነታው ግን ያሳለፍነው ጊዜ ጣፋጭነት ይወሰናል ነው፡፡

No comments:

Post a Comment