የፍቅር ምርጫዬ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ከተጀመረ
ጀምሮ የተለያየ አስተያት እየቀረበበት የሚገኝ የሰዎችን ሀሳብ በከፍተኛ የከፋፈለ እና ጎራ አስለይቶ ያጨቃጨቀ ፡፡ ገና ከጅምሩ
ብዙ ውዝግብ የታየበት ፕሮገራም ሆኑዋል፡፡
የተካራካሪዎቹ ሀሳብ ሁለት አይነት ነው፡፡ የመጀመሪያው
ግሩፕ -እኛ ልንለወጥ ይገባል፡፡ እስከመቼ ድረስ ጉዋደኛ እየተደበቀ ይኖራል፡፡ በግልጽ ስለ ጉዋደኝነት ፡ ስለፍቅር ስለወሲብ ልናወራ
ይገባል፡፡ ይህ አለመኖሩ ነው እስካሁንም በበሽታ የተጠቃነው፡፡ በቀናወራውስ የምናደርገው ይሀንኑ አይደለምን ? ብለው ይጥቃሉ፡፡
የተመራጮችን አርአያም ይበል የሚያስብል ነው ብለው ይከራከራሉ፡፡
በአን ጻሩ ያሉ ተከራካሪዎች በበኩላቸው ማንኛውም
የቴሌቪዥን ፕሮግራም ሌሎች ቻናሎች ላይ ስለታየ ብቻ ቀድቶ ማቅረብ ምንኛ እብደት ነው
ብለው ይጠይቃሉ፡፡ እንዲህ ያለው ሾው ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል፡፡ ብለው ይሞግታሉ፡፡ እስኪ ይህንን አይነት ምርጫ በየትምህርት ቤቱ
ቢከናወን እና ልጆቻችን የፍቅር ምርጫ ቢኖራቸው ምን ያህል ጉዳት ሊያደርስ እንደሚችል በማሳየት አጥብቀው ይክራከራሉ፡፡
አንዳንዶች የቴሌቪዥን ፕሮግራሙ ባስቸኩዋይ መቆም እንዳለበት አጥብቀው ይወተውታሉ፡፡
ለነገሩ የኔም አቁዋም ከሁለተኞቹ ይ ካተታል፡፡ በግል አሁን ያለን ግልጸኝነት ገና
በጣም ስላልዳበረ እንደወረደ ይህንን አያነት ሾው ባንድ ግዜ መገልበጥ እና መቅረብ አልነበረበትም፡፡ ከዚያ በፊት ትንሽ መሃከለኛ
የሆነ ነገር መቅረብ ነበረበት ብዬ አምናለሁ፡፡
እናነተስ?
No comments:
Post a Comment