Saturday, February 20, 2016

ቫላንታይን እና እኛ እና እነሱ!!




ከቅርብ ግዜ ወዲህ ከነጮቹ ከኮረጅናቸው ትውፊቶች አንዱ ቫላንታይን ነው፡፡ ቫላንታይንን ተከትሎ ሆቴሎቻችን ሽቀላ ተመችቶአቸዋል፡፡ ምግብና መጠጥን ጨምሮ ልዩ የቫላንታይን ቀን ዝግጅት በሶስት መቶ ብር ብቻ የተለመደ ማስታወቂያ ነው፡፡ ይቅርታ ይህቺ እኛ ሰፈር ያለችዋ ዋጋ ናት፡፡

እዛኛው ሰፈሮች ከሁዋላዋ አንድ ዜሮ በመጨመር ተባበሩኝ፡፡

ታድያ የቫላንታይን አካባቢ የቀይ ልብስ ሲያንስ ሲያንስ በጥፍ ሲበዛ ከዚያም በላይ ይጨምራል፡፡ ሌላ ጊዜ ጥግ ላይ ተጥላ የነበረች ቀይ ልብስ ክብር ታገኛለች የዛ ሰሞን፡፡ ብዙዎቹ ካፌዎች እና ባሮች በቀይ ቀለም ያሸበርቃሉ ፡፡ ቀይ አበባ በሌሎቹ አበቦች ላይ ትነግሳለች፡፡

ይሁንና ቫላንታይን በኪነጥበብ ሰዎች ዘንድ በየአመቱ ማጨቃጨቁዋ አልቀረም፡፡ አምርረው የሚከራከሩ ተቁአሚዎች ቫላንታይን የባህል ወረርሽኝ ነው፡፡ በፍቅር ሰበብ የተሰነዘረ የባህል ማጥፊያ ነው ሲሉ ይደመጣል፡፡ ቫላንታይንን ሰበብ በማድረግ በየመንገዱ መሳሳም ምን ይሉታል ብለው ይሞግታሉ፡፡

ሌሎች ምነው ፍቅር ቢወሳ ፍቅር ቢዘከር ስለፍቅር መስዋእትነትን እንደ ቄስ ቫላንታይን ያሉ ቢታወሱ ምን ችግር አለ ፡፡ ይህ አላስፈላጊ ወግ አጥባቂነት ነው ብለው ሲሞግቱ ይደመጣሉ፡፡ ምነው የጥምቀት ቀን ቆነጃጂት እምር ብለው ለመታየት ኮበሌውንም ለመማረክ ፡ ግፋም ሲል ከከንፈር ወዳጆቻቸው ጋርስ ሲጫወቱ ይፈቀድምላቸዋል አይደል ብለው ይሞግታሉ፡፡

ለነገሩ የሱሬውን ባትሌት ዝቅ ሳይሆን ልቅቅ አድርጎት ትርጉሙን ለማያውቀው ፡በደረቱ ላይ የ ሰማይ ስባሪ የሚያክል ሰንሰለት አጥልቆ ለምን እንዳደረገው የማያስረዳ ፡ ኮረዳዋን ይመስል ሎቲ አጥልቆ ጸጉሩን አንጨፍሮ ለምን ሲባል እኔንጃ የሚል በበዛበት በዚህ ዘመን ቫላንታይንን በጥርጣሬ ሰዎች ለምን አዩት አይባልም፡፡

ነገር ግን ሁሉም ነገር ልክ አለው ፡፡ ጥርጣሬም ልክ አለው፡፡ ለባህል መቆርቆርም ልክ አለው፡፡ ፍቅር የሁሉ ነገር ገዢነው ካልን ፡ፍቅር ከሁሉ ይበልጣል ካልን ፍቅርን የምንዘክርበት አንድ ቀን ቢኖረን ምን ይለዋል ? ምንም!! ቸር እንሰንብት፡፡

Thursday, February 4, 2016

የዘንድሮ ውፍረት!!




ድሮ ድሮ ወፈር ያሉ ሰዎችን ስናይ ስለሀብታቸው እናስብ ነበር፡፡ ፐ እንዴት ሀብታም ነው/ነች ፡፡ ውፍረት የመመቸት ዋና መግለጫ ሆኖ ቆይቱዋል፡፡
ዛሬ ዛሬ የወፍራሞች ቁጥር ያለቅጥ እየጨመረ ነው ፡፡ በየመንደሩ የ ኑሮን ሁኔታ ያላገናዘበ ውፍረት በብዛት እየታየ ነው፡፡ ውፍረት የመመቸት ሳይሆን የተስፋ መቁረጥ ምንክት እየሆነ መጥቶአል፡፡
ታድ ያ እነዚህን ሰዎች ተመቻችሁ ብትሉዋቸው በጣም ግራ ሶጋቡ ያታያል፡፡ ይልቁንም ተስፋ የመቁረጥ ምልክት እንደሆነ ያስዱዋቹሃል፡፡
ለነገሩ በ አሜሪካም ያለው ስታስቲክስ የሚያሳየው ከነጮቹ ይልቅ የ ስፓኒክ እና የጥቁር አሜሪካውያን የውፍረት መጠን መጨመሩን እና በዛው መጠን የ ሃብት ክፍፍሉ ከዚህ ጋር እንደሚጣረስ ነው፡፡

Wednesday, February 3, 2016

አሮጌ ፍንዳታዎች!!



በቅርብ በቅርብ እየበዙ የመጡ ፡ለእይታ እምብዛም የማይስቡ ነገርግን በየግላቸው አለም የሚኖሩ የሼባ ፍንዳታዎችን መመልከት የተለመደ ሆኑዋል፡፡ እነዚህ ፍንዳታዎች ከዋናዎቹ ፍንዳታዎች የሚለያቸው የሚሰሩትን የሚያውቁ የራሳቸው ህይወት ኖሮዋቸው ያለፉ እና ክፉውንና ደጉን በደምብ የሚያውቁ ፍንዳታን በግል ምርጫቸው የተቆራኙ መሆናቸው ነው፡፡
ታድያ እነዚህ ፍንዳታዎች ፤ የምር ፍንዳታ ከሆኑ ከልጆቻቸው ፡ ምናልባትም ከልጅ ልጆቻቸው እኩያዎች ጋር በየመንገዱ ልክ እንደዱሮዋቸው ሲፈነዱ ማየት ለተመልካች ቢከብድም ለነሱ ግን ምነሼ ብለውታል፡፡
ታድያ እነዚህን ሰዎች ከዚህ በፊት ከፍንዳታ በፊት የሚያውቁትን ሰው ሲያገኙ ማየት ምን ያህል እንደሚገርም ማየት ይቻላል፡፡ ባነዴ ከፍንዳታ ወደ እውቃታ ከዚያም በዚያው ፍጥነት ወደፍንዳታ ይመለሳሉ፡፡
አይኖች በብዛት እነሱ ላ ይ እነደሚያርፍ ያስባሉ ፡፡ ታድያ ያ ይመቻቸዋል፡፡ አማርኛ የጠፋባቸዋል፡፡ እንግሊዘኛ ያበዛሉ፡፡ ለነገሮች ብዙም አይጨነቁም፡፡ ላይፍን ቀጨት እያደረጉ እንደሆነ ያምናሉ፡፡ሌሎች በማያገባቸው ነገር እንደሚጨነቁ ያስባሉ፡፡ በነሱ አይን እነዛ ሰዎች ፋራዎች ናቸው፡፡
ታድያ ጉዱ እንደ ማነው ትያትር ቤቢ ቤቢሾ ሽትል ከርማ የእውነት ጸብ ሲመጣ አንተ ሽማግሌ ማነህ አቶ …….እንዳለችው ከሆነ ነው!!!

Tuesday, February 2, 2016

ስለብሎጉ መግለጫ -ትንሽ ማፍታቻ!!



አንድ ጉዋደኞቼ የብሎጌን መግለጫ ተማልክቶ ፡፡"ቦቅቡዋቃ ነህ" የሚመስስል አስተያየት አደረሰኝ እናም ምናልባት ትንሽ ታስረዳልኝ እንደሁ ብዬ ይህችን ሃተታ ለመጸፍ ተገደርኩ፡፡
እንደኔ እምነት የዚህ ሀገር የፖለቲካ ብሎጊንግ ወይ እዚህ ጥግ ወይ እዛ ጥግ ነው፡፡ መሀል የሚባል ነገር የለም፡፡ አይ ግድቡ ፡ አይ ባቡሩ ብለህ ከጻፍክ ተለጣፊ ነህ በብዙወች፡፡ የዲሞክራሳዊ ምህዳሩ ጠባብ ነው፡፡ እንደሃገር ዲሞክራሲው የምንችለውን ያህል አላደገም፡፡ ብትል ህገመንግስቱን በሃይል ለማፍረስ ያለመሞከርህን ማስረጃ ማቅረብ ሊያስፈልግህ ይችላል፡፡
በዚህ ላይ በሁለቱም ጽንፍ ከደርዘን በላይ ተያቢያን እያሉ መደረብ ምን ያደርጋል? ብዬ ነው እንጂ ብዙም ፈርቼ አይደለም፡፡
እምነት በኔ እይታ የምትኖርበት እንጂ አንዱን ካንዱ የምታበላልጥበት አይመስለኝም፡፡ በዚህ ላይ ሁሉም እምነቶች ስለመልካምነት ነው የሚያስተምሩት፡፡
ለማንኛውም ስላአስተይየቱ እንደተመቸኝ መግለጽ እወዳለሁ ይመችህ!!

Monday, February 1, 2016

የፍቅር ምርጫዬ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ፡ የዘመናዊናት መገለጫ ወይስ የባህል ወረራ አንዱ ማሳያ?





የፍቅር ምርጫዬ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ከተጀመረ ጀምሮ የተለያየ አስተያት እየቀረበበት የሚገኝ የሰዎችን ሀሳብ በከፍተኛ የከፋፈለ እና ጎራ አስለይቶ ያጨቃጨቀ ፡፡ ገና ከጅምሩ ብዙ ውዝግብ የታየበት ፕሮገራም ሆኑዋል፡፡
የተካራካሪዎቹ ሀሳብ ሁለት አይነት ነው፡፡ የመጀመሪያው ግሩፕ -እኛ ልንለወጥ ይገባል፡፡ እስከመቼ ድረስ ጉዋደኛ እየተደበቀ ይኖራል፡፡ በግልጽ ስለ ጉዋደኝነት ፡ ስለፍቅር ስለወሲብ ልናወራ ይገባል፡፡ ይህ አለመኖሩ ነው እስካሁንም በበሽታ የተጠቃነው፡፡ በቀናወራውስ የምናደርገው ይሀንኑ አይደለምን ? ብለው ይጥቃሉ፡፡ የተመራጮችን አርአያም ይበል የሚያስብል ነው ብለው ይከራከራሉ፡፡
በአን ጻሩ ያሉ ተከራካሪዎች በበኩላቸው ማንኛውም የቴሌቪዥን ፕሮግራም ሌሎች ቻናሎች ላይ ስለታየ ብቻ ቀድቶ ማቅረብ ምንኛ እብደት ነው ብለው ይጠይቃሉ፡፡ እንዲህ ያለው ሾው ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል፡፡ ብለው ይሞግታሉ፡፡ እስኪ ይህንን አይነት ምርጫ በየትምህርት ቤቱ ቢከናወን እና ልጆቻችን የፍቅር ምርጫ ቢኖራቸው ምን ያህል ጉዳት ሊያደርስ እንደሚችል በማሳየት አጥብቀው ይክራከራሉ፡፡
አንዳንዶች የቴሌቪዥን ፕሮግራሙ ባስቸኩዋይ መቆም እንዳለበት አጥብቀው ይወተውታሉ፡፡
ለነገሩ የኔም አቁዋም ከሁለተኞቹ ይ ካተታል፡፡ በግል አሁን ያለን ግልጸኝነት ገና በጣም ስላልዳበረ እንደወረደ ይህንን አያነት ሾው ባንድ ግዜ መገልበጥ እና መቅረብ አልነበረበትም፡፡ ከዚያ በፊት ትንሽ መሃከለኛ የሆነ ነገር መቅረብ ነበረበት ብዬ አምናለሁ፡፡
እናነተስ?