አንድ ጉዋደኞቼ የብሎጌን መግለጫ ተማልክቶ ፡፡"ቦቅቡዋቃ
ነህ" የሚመስስል አስተያየት አደረሰኝ እናም ምናልባት ትንሽ ታስረዳልኝ እንደሁ ብዬ ይህችን ሃተታ ለመጸፍ ተገደርኩ፡፡
እንደኔ እምነት የዚህ ሀገር የፖለቲካ ብሎጊንግ
ወይ እዚህ ጥግ ወይ እዛ ጥግ ነው፡፡ መሀል የሚባል ነገር የለም፡፡ አይ ግድቡ ፡ አይ ባቡሩ ብለህ ከጻፍክ ተለጣፊ ነህ በብዙወች፡፡
የዲሞክራሳዊ ምህዳሩ ጠባብ ነው፡፡ እንደሃገር ዲሞክራሲው የምንችለውን ያህል አላደገም፡፡ ብትል ህገመንግስቱን በሃይል ለማፍረስ
ያለመሞከርህን ማስረጃ ማቅረብ ሊያስፈልግህ ይችላል፡፡
በዚህ ላይ በሁለቱም ጽንፍ ከደርዘን በላይ ተያቢያን
እያሉ መደረብ ምን ያደርጋል? ብዬ ነው እንጂ ብዙም ፈርቼ አይደለም፡፡
እምነት በኔ እይታ የምትኖርበት እንጂ አንዱን
ካንዱ የምታበላልጥበት አይመስለኝም፡፡ በዚህ ላይ ሁሉም እምነቶች ስለመልካምነት ነው የሚያስተምሩት፡፡
ለማንኛውም ስላአስተይየቱ እንደተመቸኝ መግለጽ
እወዳለሁ ይመችህ!!
No comments:
Post a Comment