በቅርብ በቅርብ እየበዙ የመጡ ፡ለእይታ እምብዛም
የማይስቡ ነገርግን በየግላቸው አለም የሚኖሩ የሼባ ፍንዳታዎችን መመልከት የተለመደ ሆኑዋል፡፡ እነዚህ ፍንዳታዎች ከዋናዎቹ ፍንዳታዎች
የሚለያቸው የሚሰሩትን የሚያውቁ የራሳቸው ህይወት ኖሮዋቸው ያለፉ እና ክፉውንና ደጉን በደምብ የሚያውቁ ፍንዳታን በግል ምርጫቸው
የተቆራኙ መሆናቸው ነው፡፡
ታድያ እነዚህ ፍንዳታዎች ፤ የምር ፍንዳታ ከሆኑ
ከልጆቻቸው ፡ ምናልባትም ከልጅ ልጆቻቸው እኩያዎች ጋር በየመንገዱ ልክ እንደዱሮዋቸው ሲፈነዱ ማየት ለተመልካች ቢከብድም ለነሱ
ግን ምነሼ ብለውታል፡፡
ታድያ እነዚህን ሰዎች ከዚህ በፊት ከፍንዳታ በፊት
የሚያውቁትን ሰው ሲያገኙ ማየት ምን ያህል እንደሚገርም ማየት ይቻላል፡፡ ባነዴ ከፍንዳታ ወደ እውቃታ ከዚያም በዚያው ፍጥነት ወደፍንዳታ
ይመለሳሉ፡፡
አይኖች በብዛት እነሱ ላ ይ እነደሚያርፍ ያስባሉ
፡፡ ታድያ ያ ይመቻቸዋል፡፡ አማርኛ የጠፋባቸዋል፡፡ እንግሊዘኛ ያበዛሉ፡፡ ለነገሮች ብዙም አይጨነቁም፡፡ ላይፍን ቀጨት እያደረጉ
እንደሆነ ያምናሉ፡፡ሌሎች በማያገባቸው ነገር እንደሚጨነቁ ያስባሉ፡፡ በነሱ አይን እነዛ ሰዎች ፋራዎች ናቸው፡፡
ታድያ ጉዱ እንደ ማነው ትያትር ቤቢ ቤቢሾ ሽትል
ከርማ የእውነት ጸብ ሲመጣ አንተ ሽማግሌ ማነህ አቶ …….እንዳለችው ከሆነ ነው!!!
No comments:
Post a Comment